Friday, June 10, 2011

ዝምታ

 He was very humble and patient when አይሁድ did anything to him. when it comes to the church He didnt let them do whatever they want. እኛም እኮ በግል ለብዙ ጊዜ ሲሰድቡን የማይሆን ስም ሲሰጡን ሲደበድቡ ሲገድሉን እንታገስ ይሆናል ግን በቤተ ክርስቲያን ሲመጡ ግን ይህ የእዚአብሄር ቤት እንጂ የሆዳሞች የግድ የለሾች የነጋዴዎች እና የመናፍቃን ቤት አይደለም ማለት ይገባናል። ሲገርፉት ሲሰቅሉት የታገሰ ጌታ ለምን የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት ነው " የቤትህ ቅናት አቃጠለኝ" በማለት በጅራፍ አባረረ። ዛሬ በተለያዩ ሃገራት እንዲህ የሚል በመጥፋቱ የእምነት ድርጅቶች ንግድ ሆነዋል ። ጌይ ፓስተሮች፡ ከጌታ ቃል ይልቅ ለዲሞክራሲና ሥልጣኔ ያደሉ አገልጋዮች፡ ገንዘብና ስልጣን የሚያሯሩጡ መነኮሳት፡ አገልግሎታቸዉ ሙያና ችሎታ እንጂ የእግዚአብሄር ጸጋ መሆኑን የረሱ ዝናና ሃብት ያተኮሩ ሰባክያን ዘማሪያን የሞሉበት ቤተ አምልኮት ተስፋፉ። እኛም ጋር ይህ ነው እየገባ ያለው ። ያሁኖቹ በድፍረት እያወቁ ነው የሚያደርጉት ጌታ ካባረራቸው ይብሳሉ። ክርስቶስ መጥቶ በጂራፍ እንዲያባርር መጠበቅ የለብንም። ዛሬ ዝም እያልን እየተለማመድን ነገ gay and lesbians እየሆኑ ካልገባን ሲሉ እግዚአብሄር እራሱ ይስራ ልንል ነው። ታዲያ የኛ ድርሻ ምንድነው? እነ ሙሴ ዳዊት ጌጌዎን ሶምሶን እና ለሎችም ለምን ለእምልኮተ እግዚአብሄርና ለህዝባቸው እንዲጋደሉ አምላክ መርጦ አዘዛቸው? መጽሐፍ እንደሚል " ጽድቅን አውቆ ለማያደርጋት ኀጢአት ትሆንበታለች " ። እናም እኛ በክፉ ስራችን ብቻ ሳይሆን እያወቅን ባለማድረጋችን ኃጢአት እንዳይሆንብ ልንሰራ ይገባል። ዳግምኛም " የእግዚአብሄርን ሥራ በቸልታ የሚሰራ የተረገመ ይሁን" እንዲል የቤተ ክርስቲያንን ነገር በቸልታ እያየን ለሥርዓት አልበኞች ከተውን ትውልድና እምነት ጠፍቶ እርግማን እንዳይሆንብን ነቅተን ድርሻችን ልንወጣ ይገባል እላለሁ።