አባዜ

ምን ተሻለን
"ውይ አበሻ ሲባል....."  ከሚል አባዜ መቼ ወይስ ማን ነው የሚገላግለን። አበሻ በሰራው ነገር መቼ ይሆን የምደሰተው ወይንም የምንስማማው? መንፈሳውያኑ የሚደርጉት፥ ፖለተከኞች የሚያወሩትን፥ ምሁራኑየሚናገሩትን፥ እርስ በርሳችን በምንሰራው ሥራ ወይ አበሻ  ማለትን የምናቆመው መቼ ነው? ወይስ አበሻ ከመጥፎ  ነገር በቀር ምንም ነገር መስራት አይዋጣለትም  ማለት ነው? ምነው ራሳችን በራሳችን የጠላነው ምን አዜም ተደርጎብ ነው?  ከሃገሬ  ከጣሁ በኋላ ደግሞ   አበሻ የሌለበትአፓርትመንት ወይም ሰፈር፥ አበሻ የማይነዳው መኪና፥ አባሻ የማይበዛበት restaurant or coffee የምርጫቸው ዋና  መመዘኛቸው የሆኑ ሰዎች መብዛት ሁሌ እንድተክዝበት ያደረገኝ ጉዳይ ነው። ሌሎች የራሳቸውን ወገን ሰፈልጉ ይታያል ከዚህም የተነሳ የቻይና ሰፈር፥ የላቲኖች ሰፈር፥ የህንዶች ሰፈር፥ የአይሁዶች ሰፈር፥ የሱማሌ ሰፈር በየከተማው ማየት የተለመደ ነው።  በኛ  ዘንድ ግን ነግደን ለማትረፍ ወይም በሃዘንና  በችግር ጊዜ ብቻ መሰባሰብ የጤና አይመስለኝም። ለሌሎች ጉንጫችንን እስኪያመን እየፈገግን አባሻ ስናይ አንገት የምንደፋበት አባዜ  መቼ ይሆን የሚያበቃው። በተቀረ በየቤቱ በየመንደሩ 'ውይ አባሻ ሲባል' እያሉ የመኖር አባዜ  በጣም ሰልችቶናልና  እባካችሁ ከዛሬ  ጀምረን እርምጃውን ከራሳችን እንጀምር። እንደ ሰው ኅብረተሰብ ሆነን እንኑር።
 
እግዚአብሄር ይርዳን